መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 4፤2014-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአፍጋኒስታን ድጋፍ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ያስፈልገኛል ሲል አስታወቀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አፍጋኒስታን ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ እንዳጋጠማት በማስጠንቀቅ ከ 600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስታዉቋል፡፡ድርጅቱ ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ እንዲደረግለት ያቀረበው ጥሪ በጄኔቫ በተካሄደ ጉባሄ ላይ ሲሆን ባለፈው ወር በታሊባንን ቁጥጥር ስር አፍጋኒስታን መግባቷ የረድኤት ድጋፍ ፈላጊዎች ቁጥር ጨምሯል፡፡

ዋና ጸሐፊዉ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከዓመታት ጦርነት ፣ መከራ እና አለመረጋጋት በኋላ አፍጋኒስታኖች በጣም አደገኛ ወቅትን ይጋፈጣሉ ብለዋል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ 606 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ዕቅዱ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች አስፈላጊ እፎይታ ያመጣል ብሏል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከሦስቱ አፍጋናዉያን መካከል አንዱ ምሳ ከበላ በኃላ እራት ከየት እንደሚመጣ አያውቅም ፣ የድህነት መጠኑ እየተባባሰ እና መሠረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ወደ ውድቀት መቃረባቸዉን ድርጅቱ አስጠንቅቋል፡፡በአሁኑ ወቅት 3.5 ሚሊዮን ሰዎች በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሲሆን ከባድ የድርቅ አደጋ በሀገሪቱ ላይ ተደቅኗል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *