መደበኛ ያልሆነ

ዛሬ መስከረም 19፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ በመላዉ ዓለም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን መብለጡን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት አመላከተ፡፡ከፍተኛ የሞት መጠን የተመዘገበባቸዉ ሶስት የአለም ሀገራት አሜሪካ፣ብራዚልና ህንድ ናቸዉ፡፡

~ ከደቡብ አፍሪካ በህገወጥ መልኩ ሲንቀሳቀስ የነበረ የዱር እንስሳት ቆዳ በደቡብ ሱዳን በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ፡፡ከ320 ኪ.ግ በላይ እንደሚመዝን የተነገረ ሲሆን መዳረሻዉ ወደ አዉሮጳ ሀገራት እንደነበረ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

~ በቶጎ ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሆኑት ናንሲግቤ የሴት ጠቅላይ ሚንስትር መሾማቸዉ ተሰማ፡፡የቶጎ አዲሷ ጠቅላይ ሚንስትር ቪክቶሪያ ቱሜጋህ ናቸዉ፡፡

~ በኬንያ ከስድስት ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የምሽት የመዝናኛ ክለቦች በዛሬዉ እለት ክፍት እንደሚደረጉ ይፋ ሆነ፡፡ትምህርት ቤቶች ተዘግተዉ እንዲቆዩ ዉሳኔ ተላልፏል፡፡

~ በኢራቅ የታጠቁ ሀይሎች በፈጸሙት የሮኬት ጥቃት አምስት ሰዎች መገደላቸዉ ተሰማ፡፡ጠቅላይ ሚንስትር መስጠፋ አል ካዳሂም ከጥቃቱ ጀርባ ያሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ለጸጥታ አካላት መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡

~ በአዘርባጃንና አርሜንያ መካከል ለሁለተኛ ቀን የድንበር ግጭት መቀጠሉ ተሰማ፡፡የናጎርኖ ካራባክ የድንበር ዉዝግብ ዘመናት ያስቆጠረ ዉጥረት ሲሆን ለአዘርባጃን በተወሰነዉ ግዛት ላይ የአርሜንያ ዜጎች ይኖሩበታል መባሉ ቀዉስን ፈጥሯል፡፡

~ እስራኤል የፍልስጤም ዜግነት ያለዉን የ17 ዓመት ወጣት በአምስት ዓመት እስር መቅጣቷ ቁጣ አስነሳ፡፡በእስራኤል ማረሚያ ቤቶች እድሜያቸዉ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ከ40 ያላነሱ ፍልስጤማዉያን ያሉ ሲሆን በእስራኤል ደህንነት ላይ ስጋት ደቅናችኃል የሚለዉ የክሱ ዝርዝር ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *