መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 15፤2016 – አሚጎስ ብድር እና ቁጠባ ለ17 የላዳ አሽከርካሪዎች አዳዲስ መኪናዎችን አስረከበ

   ????አሚጎስ ብድር እና ቁጠባ  ካፒታሉን  ከ1.5 ቢሊየን ብር  በላይ አድርሷል

አሚጎስ ብድር እና ቁጠባ ለ3ኛ ዙር ለላዳ መኪና አሽከርካሪዎች የመኪናውን 30 በመቶ ለቆጠቡ 17 አሽከርካሪዎች አዳዲስል ተሽከርካሪዎችን አስረክቧ።

የአሚጎስ ብድር እና ቁጠባ የኮርፖሬት ሴልስ ዲፓርትመንት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው በኃይሉ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን እንደተናገሩት 35 የላዳ ማህበራት ከተቋሙ ጋር ውል አስረዋል ብለዋል ።

የመኪናውን  ዋጋ 30 በመቶ መቆጠብ የቻሉ 17 የላዳ አሽከርካሪዎች ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ የሚያስመጣቸው መኪኖችን እንዳስረከቡም ገልፀዋል።የብድር የክፍያ ጊዜውም ለ10 ዓመታት እንደሚቆይ እና የወለድ መጠኑም ከ9 እስከ 15 በመቶ እንደሆነም ተናግረዋል።

በ11 ዓመት ውስጥ 3ሺ ለሚሆኑ ሰዎች የብድር አቅርቦት እንደሰጠ እና ከነዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ለተሽከርካሪ መግዣ የተሰጡ ናቸው ብለዋል።አሁን ላይ አሚጎስ 1.5 ቢሊየን ብር ካፒታል ላይ መድረሱን አቶ እንዳልካቸው  በሀይሉ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

በምህረት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *