መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 15፤2016- በሰርቢያ የመንግስት ተቃዋሚዎች የቤልግሬድ ከተማን ማዘጋጃ ቤት ጥሰው ለመግባት ሞከሩ

በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ ባለገው ሳምንት የተካሄወው ምርጫ ተጭበርብሯል ያሉ ተቃዋሚዎች ያደረጉትን ሰልፍ ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሞ ለመበተን ችሏል። ከከተማው ማዘጋጃ ቤት ውጪ ከነበሩት ሰዎች መካከል የተወሰኑት መስኮቶችን ሰባብረው ወደ ውስጥ ለመግባት ከሞከሩ በኋላ ፖሊስ ጣልቃ ገብቷል። ተቃዋሚ የሆኑ የመብት ተሟጋቾች እሁድ እለት ፖሊስ ከመጠን ያለፈ ሃይል ተጠቅሟል ሲሉ ተናግረዋል።

ገዥው ፓርቲ ያሸነፈውን ምርጫ አጭበርብሮታል ሲሉ ሰልፈኞች ከሰዋል። ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ቩቺች ክሱ “ቆሻሻ እና ውሸት ነው” ብለዋል። የአረንጓዴው-ግራኝ ግንባር ተባባሪ መሪ ራዶሚር ላዞቪች እኔን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሰዎች በፖሊስ መኮንኖች መደብደባቸውን ተናግረዋል።ካለፈው ሳምንት የሀገር አቀፍ እና የአካባቢ ምርጫዎች ጀምሮ በየምሽቱ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። እሑድ እለት ግን ወደ ሁከት መለወጡን ተናግረዋል።

የሰርቢያ የተቃዋሚዎች ጥምረት ወደ ከተማው ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ለመግባት ሞክረዋል። ሰርጃን ሚሊቮጄቪች እና ቭላድሚር ኦብራዶቪች የተባሉት የተቃዋሚ መሪዎች የሕንፃውን በር ለመክፈት ሞክረዋል። ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመመከት አስለቃሽ የበርበሬ ስፕሬን ተጠቅሟል።ተቃዋሚዎቹ እንደሚሉት በቤልግሬድ የከተማ ምርጫ ላይ መንግስት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በአውቶቢስ አጓጉዞ በማምጣት ድምጽ እንዲሰጡ አድርጓል በማለት ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

በምርጫው ሂድት የቩቺች የሰርቢያ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ በፓርላማ አብላጫ ድምፅ በማግኘት ወደ ስልጣን መመለሱን ተመላክቷል። የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ሥርዓተ አልበኝነት በምርጫው ወቅት እንደነበረ ይፋ አድርገዋል። የድምጽ መስጫ ሳጥን መጨናነቅ እና ድምጽን ለመግዛት ሙከራዎች እንደነበሩ ገልፀዋል። እሁድ አመሻሽ ላይ ለህዝቡ ቩሲች ባደረጉት ንግግር ብጥብጡ የውጭ ጣልቃገብነት ነው ሲሉ ወቅሰዋል።ቩቺች አመፅን ለመዋጋት ቃለ መሃላ በመግባት የወሮበላዎች ድርጊት መሆኑን ገልፀዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *