መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 15፤2016- የመኪና ማንሻ ክሪክ የሰረቀው ተከሳሽ በ6 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን  አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር  ሁለት ሺህ ብር የሚገመት የመኪና ማንሻ  የሰረቀዉ ተከሳሽ በ6 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ተነግሯል ።

ተከሳሽ ዘሪሁን ውብሸት ህዳር 2 ቀን 2016 ዓ.ም  ከሌሊቱ 9 ሰዓት ተኩል ገደማ  የግል ተበዳይ  አ/ቶ ፀጋዬ ቦጋለ ንብረት የሆነ የመኪና ማንሻ ክሪክ መስረቁ ተገልጿል ።

ሆኖም ተከሳሽ የሰረቀውን ንብረት ይዞ ለማመለጥ ሲሞክር ፖሊስ በክትትል ከተሰረቀዉ ንብረት ጋር እንደያዘው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ።

በዚህም መሠረት ዓቃቤ ህግ የመሰረተዉን ክስ የተመለከተዉ የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።

ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ዘሪሁን ውብሸትን ያርማል ሌላውን ማህበረሰብ ያስተምራል በሚል በማረሚያ ተቋም ዉስጥ ለህግ ታራሚዎች በአመክሮ የሚቀነስ የእስር ጊዜ እንዳይሰጠዉ በማገድ በ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *