መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 15፤2016- የክርስቶስ የትውልድ ቦታ በሆነችው ቤቴልሄም ከተማ የገና በዓል ስነስርዓት ተሰረዘ

በክርስቶስ የትውልድ ከተማ ቤቴልሄም የዘንድሮ የገና አከባበር የተሰረዘ ሲሆን በተለምዶ መንገር ተብሎ የሚጠራው አደባባይን የሚሞሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶች እና ምዕመናን አልተገኙም። ከተማዋ ከደስታ፣ ከልጆች እና ከገና አባት ፀድታ ባዶ ሆናለች። በዚህ ዓመት ምንም አይነት በዓል የለም ስትል በዌስት ባንክ ቤተልሔም  ከተማ ነዋሪ የሆነችው ማዴሊን ተናግራለች።

በመኃል አደባባይ ይሰራ የነበረው የገና ዛፍ እንዳልተረሰራና ዝማሬዎች እንደማይደመጡ ብሎም የገና ገበያ እንደሌለ ገልጻለች።በአሻንጉሊት የክርስቶስን ልደይዓት በሚያሳይ ምልክት በትላልቅ ቋጥኝ ድንጋዮች እና በሽቦ የተከበበ ህፃንን በማመላከት በጋዛ የሚገኙ ልጆች የሚደርስባቸውን ጥቃት ለማሳየት ሞክረዋል። ባልተለመደ ሁኔታ ባዶ በሆነችው የክርስቶስ ልደት ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ አባ ኢሳ ታልጂያ እንደተናገሩት በዚህች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለ12 ዓመታት ካህን ሆኜ አገልግያለሁ፤ የተወለድኩት በቤተልሔም ነው ከተማ ነው፤ እንደዚህ ዓይነት መቀዛቀዝ አይቼ አላውቅም ብለዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ እንኳን እንዲህ ዓይነት ነገር አልገጠመንም ብለዋል። በጋዛ ውስጥ ያሉ ወንድሞች እና እህቶች ያሉበት ሁኔታ በዓሉን ለማክበር አስቸጋሪ የሚያደርገው ነው ብለዋል። ጃዋዳት ሚካኤል የሚባል የቤተልሔም ከተማ ነዋሪ ቤተሰቦቼ በሰሜን ጋዛ ወጥመድ ውስጥ ይገኛሉ። በእስራኤል ጥቃት አያቴ እና አክስቴ ተገድለዋል ሲል አክሏል። በቤተልሔም አንዳንድ የነዋሪዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በሚያስመለክቱ ነገር ግን ፍርስራሽ በተሞሉ ስፍራ ዝማሬዎችን በመዘመር ሰላም ለህፃናት እያሉ ጥሪ ሲያደርጉና የቤተክርስቲያን ደወል ሲደወል ይሰማል።

በርካታ ሰዎች ትልቅ የፍልስጤም ባንዲራ ይዘው ሲያውለበለቡ ታይተዋል። የኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ አድራሾች ውስጥ በቤተልሔም ባህላዊውን ጥቁር እና ነጭ የፍልስጤም ማህበረሰብ ልብስ ፓትርያርኩ ለብሰው ታይተዋል። ይህ በጣም የሚያሳዝን የገና በዓል ነው ሲሉ ፓትርያርኩ ተናግረዋል ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *